Ethiopia’s human rights record to be examined by Universal Periodic Review
07 November 2024
The human rights record of Ethiopia will be examined by the United Nations Human Rights Council’s Universal Periodic Review (UPR) Working Group for the fourth time on Tuesday, 12 November 2024, in a meeting in Geneva that will be webcast live.
Ethiopia is one of 14 States to be reviewed by the UPR Working Group during its upcoming session from 4 to 15 November 2024. The first, second and third UPR reviews of Ethiopia took place in December 2009, May 2014, and May 2019, respectively.
The UPR Working Group is comprised of the 47 Member States of the Human Rights Council. However, each of the 193 UN Member States can participate in a country review.
The documents on which the reviews are based are: 1) national report - information provided by the State under review; 2) information contained in the reports of independent human rights experts and groups, known as the special procedures, human rights treaty bodies, and other UN entities; 3) information provided by other stakeholders including national human rights institutions, regional organizations, and civil society groups.
The three reports serving as the basis for the review of Ethiopia on 12 November can be found here.
Location: Room 20, Palais des Nations, Geneva.
Time and date: 9:00 – 12:30, Tuesday, 12 November 2024 (Geneva time, GMT+1).
The UPR is a peer review of the human rights records of all 193 UN Member States. Since its first meeting was held in April 2008, all 193 UN Member States have been reviewed thrice. During the fourth UPR cycle, States are again expected to spell out steps they have taken to implement recommendations posed during their previous reviews which they committed to follow up on and highlight recent human rights developments in the country.
The delegation of Ethiopia will be led by Belayihun Yirga Kifle, State Minister, Ministry of Justice.
The three country representatives serving as rapporteurs (“troika”) for the review of Ethiopia are Algeria, Bangladesh, and the Kingdom of the Netherlands.
The webcast of the session will be at: https://webtv.un.org/en/asset/k1v/k1v9l03wc8
The list of speakers and all available statements to be delivered during the review of Ethiopia will be posted on the UPR Extranet.
The UPR Working Group is scheduled to adopt the recommendations made to Ethiopia on Friday, 15 November 2024, between 16:00 and 18:00 (GMT+1). The State under review may wish to express its positions on recommendations posed to it during its review.
// ENDS //
For more information and media requests, please contact Pascal Sim, HRC Media Officer, at simp@un.org, David Díaz Martín, HRC Public Information Officer at david.diazmartin@un.org, and Matthew Brown, HRC Public Information Officer, at Matthew.Brown@un.org
To learn more about the Universal Periodic Review:
www.ohchr.org/en/hr-bodies/upr/upr-main
Sign up for the UN Human Rights Council Newsletter:
https://mailchi.mp/a3a538479938/hrc-mailshot-to-ohchr-global
Follow us on social media:
Facebook | X | YouTube | Instagram
Amharic version:
ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ በተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ግምገማ ሊደረግበት ነው
ጄኔቫ (ጥቅምት 28 2017 ዓ.ም): የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ በአራተኛው ዙር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ( (ዩ.ፒ.አር) መድረክ ላይ ግምገማ ሊደረግበት ነው፡፡ የግምገማ ቡድኑ ስብሰባውን ማክሰኞ ህዳር 3 ቀን 2017 በጄኔቫ የሚያደርግ ሲሆን ስብሰባው በቀጥታ በድህረ ገጽ (ዌብ ካስት) ይተላለፋል።
ኢትዮጵያ ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው የግምገማ መድረክ ላይ ከሚገመገሙት 14 ሀገራት ውስጥ ትገኛለች :: የኢትዮጵያ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዙር ግምገማዎች በታህሳስ 1995 ዓ.ም ፣ በግንቦት 1998 ዓ.ም እና በግንቦት 2001 ዓ.ም በቅደም ተከተል ተካሂደዋል።
የግምገማ ቡድኑ 47 የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራትን ያቀፈ ቢሆንም አንድ መቶ ዘጠና ሶስቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት በሀገራት ግምገማው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
የሀገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ በሚከተሉት ሰነዶች ላይ ተመስርቶ ይከናወናል ፦
- ሀገራዊ ሪፓርት;-እየተገመገመ ባለው ሀገር የሚቀርብ ሀገር አቀፍ ሪፖርት
- ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች እና ቡድኖች ሪፖርቶች ፤ሀገራት በተቀበሉት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ዙሪያ ክትትል የሚከናውኑ አካላት እንዲሁም ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ሪፖርቶች ውስጥ የተካተቱ መረጃዎች
- ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን ጨምሮ በሌሎች ባለድርሻ አካላት በቀረቡ መረጃዎች ናቸው፡፡
ኢትዮጲያን ለመገምገም መሰረት የሚሆኑት እነዚህ ሶስት ሪፖርቶች በዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ ይገኛሉ https://www.ohchr.org/en/hr-bodies/upr/et-index
ቦታ: ጄኔቫ ፓሌ ደ ናሲኦን ክፍል ቁጥር 20
ሰዓት፡ 5፡00 – 8፡30 (በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር)
ቀን፡ ማክሰኞ ህዳር 3 2017
የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ አንድ መቶ ዘጠና ሶስቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት የእርስ በራሳቸው ግምገማ የሚያደርጉብት መድረክ ነው። የመጀመሪያው ስብሰባ በሚያዚያ 2000 ዓ.ም ከተካሄደ ጀምሮ አንድ መቶ ዘጠና ሶስቱም የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት ለሶስት ጊዜ በመድረኩ ተገምግመዋል። በአራተኛው ግምገማ መንግስታት በቀደሙት ግምገማዎች ላይ የቀረቡላቸውን ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ የወሰዷቸውን እርምጃዎች እና በየሀገራቱ ውስጥ ያሉ የቅርብ ጊዜ የሰብአዊ መብት (አያያዝ) ሁኔታዎችን እንዲገልጹ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፍትህ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ ክፍሌ ይመራል።
የኢትዮጵያን ግምግማ ሂደት አከናዋኞች ሆነው የተሰየሙት የአልጄሪያ፣ ባንግላዲሽ እና የኔዘርላንድ መንግሥታት ተወካዮች ናቸው።
የግምገማው ሂደት ድህረ ገጽ https://webtv.un.org/en/asset/k1v/k1v9l03wc8
በኢትዮጵያ ግምገማ ወቅት የሚቀርቡት የተናጋሪዎች ዝርዝር እና በግምገማው ዙሪያ የሚሰጡ ሁሉንም መግለጫዎች በሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ መድረክ መረጃ ቋት (UPR Extranet) ላይ ይቀመጣሉ፡፡
የግምገማ ቡድኑ በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚሰጡትን ምክረ ሀሳቦች አርብ ህዳር 6 ቀን 2017 ከቀኑ 12፡00 እስከ 02፡00 ባለው ጊዜ የሚያጸድቅ ሲሆን እየተገመገመ ያለው ሀገር በግምገማው ወቅት በሚቀርቡለት ምክረ ሀሳቦች ላይ አቋሙን መግለጽ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ እና የሚዲያ ጥያቄዎች፣ እባክዎን
ፓስካል ሲም፣ የሚዲያ ኦፊሰርን simp@un.org
ዴቪድ ዲያዝ ማርቲን፡ የህዝብ መረጃ ኦፊሰር david.diazmartin@un.org እና
ማቲው ብራውን፣ የህዝብ መረጃ ኦፊሰር Matthew.Brown@un.org ያነጋግሩ
ሰለ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ መድረክ የበለጠ ለማወቅ ከታች ያለውን ድህረ ገፅ ይመልከቱ
www.ohchr.org/en/hr-bodies/upr/upr-main
ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መጽሄት ከዚህ በታች ባለው ድህረ ገፅ ይመዝገቡ
https://mailchi.mp/a3a538479938/hrc-mailshot-to-ohchr-global
Facebook | X | YouTube | Instagram